3. የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጄክት        
 3.1 የፕሮጄክቱ ቦታ
የወለህ ደብረ-ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በዋግ ኽምራ መስተዳድር ዞን በሰቆጣ ወረዳ የምትገኝ ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ወለህ ከአዲስ አበባ 682 ኪ.ሜ.፤ ከዞኑ ዋና ከተማ ከሰቆጣ ደግሞ 18 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ ሜዳማ ቀበሌ ነው፡፡ ቦታው ወይናደጋማ የአየር ንብረት አለው፡፡


ወለህ ከኮረም ወደሰቆጣ በሚወስደው መንገድ ላይ ገባ ብላ እንደመገኘቱ መጠን በተወሰኑ መልኩ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ ነው፡፡ክሊኒክ፣አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤ/ት ፣ መብራት ፣ የመጠጥ ውሃና ጥርጊያ መንገድ አካባቢው ተጠቃሚ የሆነባቸው የልማት  ውጤቶች ናቸው:: 

3.2 የትምህርት ይዘት
ት/ቤቱ መሠረታዊውን የአብነት ትምህርት(ንባብ፣ ውዳሴ ማርያም፤ዳዊትእና መልክኦችን ወ.ዘ.ተ.) የአጠናቀቁትን በመጻሕፍት ትርጓሜ ያሰለጥናል:: የመጻሕፍት ትርጓሜ  የሚባለው የብሉይ ፣ የሐዲስ ፣ የመጽሐፈ ሊቃውንትና የመጽሐፈ መነኮሳትን ትርጓሜ  ነው:: ከአብነቱ ትምህርት ጎን ለጎን ለሃዋሪያዊ ተልእኮ የሚያበቃቸውን ተጨማሪ መሠረታዊ ትምህርቶች ያስተምራል።እነዚህም ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን፤የቤተክርስቲያንታሪክ፤ሥርዓተቤተክርስቲያን፤ሥርዓተ-ኖሎት፤ግእዝ፤አስተዳደር፤ጤና አጠባበቅ እና ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ናቸው።

3.3 ግንባታ
በመግቢያው ላይ በታየው ስእላዊ መግለጫ መሰረት ፕሮጄክቱ የሰባት ህንጻዎችን ግንባታ ያጠቃልላል ::እነዚህም፦

  • መማርያ ህንጻ         5.  አስተዳደር ህንጻ
  • መኝታ ህንጻ          6. ጥበቃ ክፍል እና
  •  መመገቢያ ህንጻ     7. መጸዳጃ ቤት  ናቸው::
  • እንግዳ መቀበያ

Comments powered by CComment

ስብከቶች (Preaching)

  • 7222

    ሉቃስ ወንጌል ም። 18 ቁ። 1 __6

    1ሳይታክቱ ዘወትር  ሊጸልዩ  እንዲገባቸው የሚል ምሳሌ ነገራቸው፤ 2እንዲህ ሲል፤  “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። 3በዚያችው ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች፣ ‘ከባላጋራዬ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር።  4 አያሌ ቀንም አልወደደም ፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፤ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላፍር፣ 5ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፣ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ  እፈርድላታለሁ አለ።’  6ጌታም አለ፤ “ዓመፀኛው ዳኛ...

  • 5727

    ቀሲስ ሕብረት የሺጥላ፣ በስብከታቸው ከዚህ በታች ያሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን ያብራራሉ፤ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (link ) በመጫን ስብከቱን ያድምጡ።

    1. የመላእክት አፈጣጠር
    2. የመላእክት ቁጥር ሰንት ነው?
    3. መላእክት ሰራቸው ምንድን ነው ?
    4. ማማለድ ምን ማለት ነው 

  • 5774

    (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከነዚህ ነገሮች ቦኃላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፣ እንሆ አለሁ አለ። የምትወደውን አንድ ልጅህን ይሥሀቅን ይዘህ ወደሞርያም ምድር ኺድ እኔም በምነግርህ ባንድ ተራራ ላይ በዚያ ምሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ። አብርሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፣ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሐቅን ከርሱ ጋር ወሰደ፣ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።  (ኦሪት ዘፍጥረት ም.22  ቁ. 1.)

    ከዚህ ኃይለቃል...

  • 5739

    ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው። እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው። ማቴዎስወንጌል ም. 4 ቁ - 1

    ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት ቀሲስ ሕብረት...

  • 4811

    "እንሆ የእህትሽ የሰዶም ኀጢአት ይህ ነበረ። ትዕቢት ፣ እንጀራን መጥገብ ፣ መዝለልና ሥራ ምፍታት በርሷና በሴቶች ልጆቿ ነበረ ፣ የችግረኛውንና የድሃውንም እጅ አላጸናችም። " ሕዝቃኤል 16 ቁጥር 42

    ቀሲስሕብረትየሺጥላ፣ ከዚህ ኃይለቃል በመነሳት፣በስብከታቸውከዚህበታችያሉትንእናሌሎችጥያቄዎችን...

    Read more: የሰዶም ኀጢአት

  • 1866

    የያቆብ መልእክት

    በመከራ ላሉ የተሰጠ የተስፋ መልእክት።

    {youtube}https://youtu.be/ss8oae-j8lQ{/youtube}

    {youtube}https://www.youtube.com/watch?v=ss8oae-j8lQ{/youtube}

     

ማስታወቂያዎች

Login Form