-
Details
-
Written by: ዳንኤል ሽፈራው
-
Hits: 3539
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ::
‘ቤተክርስቲያናችን ተማሪ አስተምሪ አንድነት ስላሉሽ መሪና ተመሪ ‘
በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ወለህ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚቴ
1 መግቢያ
"ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ ወለሊቃውንቲከ ይዜንዉከ፤
አባትህን፡ጠይቅ፡ይነግርሃል፤ሊቃውንትህንጠይቅይነግሩህማል፡፡"ዘዳ.32፤7
ወላጅ አባት ለልጅ እያበላ እያጠጣ እያለበሰ እየጠበቀ ያሳድገዋል፡፡ ለዕድሜና ለአእምሮው እየመጠነም የሚጠቅመውንና የሚጐዳውን እንዲለይ ያስረዳዋል፡፡ ስለዚህም አዲስ ነገር ሲገጥመው አባቱን ይጠይቃል፡፡
በመንፈሳዊ ሕይወትም እንዲሁ ነው፡፡ በቀለምና በቃለ እግዚአብሔር የሚወልዱን መምህራን አባቶች ይባላሉ፡፡ ስለዚህም ነው ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ “አባትህን ጠይቅ ይነግርሃል፤ ሊቃውንትህን ያስረዱሃል” የሚለው፡፡ ለመጠየቅ ግን መጀመሪያ የሚጠየቁት መኖር አለባቸው፡፡ የሚጠየቅ ከሌለ መጠየቅ የሚፈልግስ ማንን ሊጠይቅ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተጠያቂዎች ሊቃውንት መገኛ ምንጮች ደግሞ የአብነት ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ትምህርት ቤቶች በሚገባቸው መጠን ካሉ አበው ሊቃውንትን በማፍራት ለአባትነት መዓርግ አብቅተው ይሰጡናል፡፡ ያን ጊዜ እኛ መጠየቅ እንችላለን፤ የምንፈልገውንም ምግብና /መንፈሳዊ ጸጋ/አግኝተን በነፍስ በስጋ እንለመልማለን፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አብነት ትምህርት ቤቶች ለረጅም ዘመናት የሶስቱም ዘርፎች መሪዎች መገኛ ምንጮች ነበሩ፡፡
Read more: መግቢያ